Fana: At a Speed of Life!

ዶ/ር ሂሩት ካሳው በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደርን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶ/ር ሂሩት ካሳው ዛሬ ከሰዓት በኋላ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ዞዋ ዘሂዋንን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

ሁለቱ ሀገራት የቆየ ታሪካዊ የህዝብ ለህዝብ ትስስርና ከ50 አመት የዘለለ ዳፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያላቸው መሆናቸው በዚህ ወቅት ተገልጿል።

ሚንስትሯ ቻይና ዋነኛዋ የኢትዮጵያ የልማት አጋር መሆንዋን ለአምባሳደሩ የገለጹላቸው ሲሆን በባህል ቱሪዝምና ስፖርት ዘርፎች በጋራ ተጠቃሚነት ላይ የተመሰረቱ ትብብሮችን በማጠናከር የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ ስለመሰማማታቸው ከባህልና ቱሪዝም ሚንስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.