የሀገር ውስጥ ዜና

የአፍሪካ ቀን እየተከበረ ነው

By Meseret Awoke

May 25, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የአፍሪካ ቀን በአዲስ አበባ እየተከበረ ይገኛል፡፡

ቀኑ የአፍሪካ ህብረት በ1963 መመስረትን ተከትሎ ነው የሚከበረው፡፡

የአፍሪካ ቀን በተለያዩ ሃገራት እንዲሁም በአዲስ አበባ በተለያዩ መርሃ ግብሮች እየተከበረ ነው፡፡

በመርሃግብሩ የአፍሪካ ስነጽሁፍ፣ ስዕል፣ ቅርስ እና ታሪክ የሚገልጹ ስነ ጥበባዊ ሁነቶች ለዕይታ ቀርበዋል፡፡

ቀኑን አስመልክተው የሩሲያ ፕሬዚደንት፣ የቱርክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሜቭሉት ቻቩሶግሉን ጨምሮ የተለያዩ የሃገር መሪዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመርሃ ግበሩ የሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶችን ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ህይወት ሃይሉ፣ መቀመጫቸውን አዲስ አበባ ያደረጉ አምባሳደሮች እና የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ ጥሪ የተደረገላቸው አካላት ተገኝተዋል፡፡

በአብዱልሃሚድ ሙሃመድ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!