Fana: At a Speed of Life!

የሃይማኖት መሪዎች መልካም ትውልድን የመቅረፅ ስራን ማጠናከር አለባቸው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሃይማኖት መሪዎች ትውልዱ መልካሙን መንገድ እንዲከተል የመቅረፅ ስራን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ተመለከተ።

የሃይማኖት ተቋማቱ  ለሁለት ቀናት የሚቆይ በሰላም ግንባታ፣ ተግዳሮቶችና መፍትሄዎቻቸው ዙሪያ የሚመክር  መድረክ ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ ተጀምሯል።

የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ወይዘሮ ፍሬዓለም ሽባባው ÷ ሀገሪቱ የተጋረጠባትን ፈተና በብቃት እንዲትወጣና የያዘችውን ተስፋ ማሳካት እንዲትችል የሃይማኖት መሪዎችና ተቋማቱ በትብብር መስራት ይጠበቅባቸዋል ብለዋል።

ህብረተሰቡ በተለይም ወጣቱ ትውልድ መልካሙን እንዲከተል፣ ስለ ሀገራቸው ሰላምና አንድነት በጋራ እንዲተጉ የመቅረፅ ስራ ከሁሉም ቅድሚያ ሰጥተው ማጠናከር እንዳለባቸው አመልክተዋል።

የሁሉም ሃይማኖቶች መንፈሳዊ መሪዎች ሀገሪቱ አሁን ያለችበትን ወቅታዊ ሁኔታ በአግባቡ በመረዳት ፈተናዎችን ለማለፍ በጋራ የሚቆሙበት ወቅት ነው ብለዋል።

የህዳሴ ግድብ እና ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በስኬት እንዲጠናቀቅ የድርሻቸውን እንዲወጡም ተናግረዋል።

የተሳሳቱ ግለሰቦችም ሆኑ ቡድኖች ወደ መልካሙ እንዲመለሱ፣ በሰላም ግንባታ የድርሻቸውን እንዲወጡና ሊኖሩ የሚችሉ ተግዳሮቶችን በብልሃት ለማለፍ አጋዥ የመሆን ከሃይማኖት ተቋማትና መሪዎቻቸው ይጠበቃል ብለዋል።

በተለይ የህዳሴ ግድብ ማንንም በማይጎዳ መልኩ እየተሰራ እያለ ጠላት የተፈጥሮ ሀብታችን እንዳንጠቀም ለተቀን እየሰራ ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታዋ ÷አሁን ሀገራዊ አንድነትን ይበልጥ ማጠናከር ያለበት ወቅት መሆኑን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ስድስኛው ጠቅላላ ምርጫ የሀገሪቱን ቀጣይ ዕድል እጅጉን የሚወስን በመሆኑ ሁሉም ወደ ስነልቦናው በመመለስ ሀገርን የማስቀጠል ሃላፊነት በጋራ መወጣት እንደሚገባም አመልክተዋል።

በብሔርና ሃይማኖት መካከል በሚፈጠረው ግጭት ብዙዎች ለጉዳት መዳረጋቸውን የገለጹት ደግሞ የኢትዮጵያ ሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምክትል ፀሐፊ ሃጂ ማዓሱድ አደም ናቸው።

ሁለተኛው ዙር የህዳሴው ግድብ የውሃ ሙሌትና ምርጫው በሰላም እንዲጠናቀቅ በፀሎት ማጋዝ ይገበናል ብለዋል።

በተለይ ምዕመናኑን በመምራት የተረጋጋ መንፈሳዊ ሁኔታ ውስጥ እንዲገኙ ከማድረግ አንፃር ከተቋማቱ ብዙ መስራት እንደሚጠበቅም አመልክተዋል።

የሃይማኖት ተቋማቱ አሁን የሚታይባቸውን ውስጣዊና ውጫዊ ፈተናዎችን በፅናት በማለፍ በመካከላቸው መከባበር፣ ፍቅር፣ ህብረትና አንድነት ጎልቶ እንዲወጣ የድርሻችንን መወጣት አለብን ብለዋል።

መድረኩ የሃይማኖት ተቋማቱ በሰላምና አብሮነት ውስጥ እየገጠማቸው ያለውን ፈተናዎች በአንድነት ለማለፍ ቀጣይ የመፍትሔ አቅጣጫ የሚያስቀምጡበት መሆኑን ኢዜአ ዘግቧል።

የምክክር መድረኩ ለሁለት ቀናት የሚቆይ የሚቆይ ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.