ዓለምአቀፋዊ ዜና

አፍሪካ የተሻለ ሰላም አንድነትና ብልጽግና እንዲኖራት ቁርጠኛ ልንሆን ይገባል – የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር

By Meseret Awoke

May 25, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 17፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)አፍሪካ የተሻለ ሰላም አንድነት እና ብልጽግና እንዲኖራት ከመቼውም ጊዜ በላይ ቁርጠኛ ልንሆን ይገባል ሲሉ የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳፋኪ መሃመት ተናገሩ፡፡

የአፍሪካ ህብረት ኮሚሽን ሊቀመንበር ሙሳ ፋኪ መሃመት የአፍሪካ ቀንን አስመልክተው መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በመልዕክታቸውም አፍሪካ የተሻለ ሰላም፣ አንድነትና ብልጽግና እንዲኖራት ቁርጠኝነት ሊኖረን ይገባል ሲሉ በትዊተር ገጻቸው አስፍረዋል፡፡

ሊቀመንበሩ ጨምረውም አንድነታችን ትልቁ የጥንካሬያችን ምንጭ ነው ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!