የሀገር ውስጥ ዜና

እኔም ለወገኔ በስዊዘርላንድ የበጎ አድራጎት ማህበር በአጣዬ አካባቢ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አደረገ

By Meseret Awoke

May 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) እኔም ለወገኔ በስዊዘርላንድ የበጎ አድራጎት ማህበር በአጣዬ አካባቢ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ አድርጓል፡፡

ማህበሩ በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን በኤፍራታና ግድም፣ በቀወት፣ በአንጾኪያ ገምዛ ወረዳዎች እና በኦሮሞ ብሄረሰብ አስተዳደር ዞን አዋሳኝ አካባቢዎች በደረሰው ውድመት ንብረታቸው ለወደመባቸውና ለተፈናቀሉ ንጹሃን ዜጎች የሚሆን 715 ሺህ ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

ከዚህ በፊት ማህበሩ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ የ30 ሺህ ዶላር ቦንድ እንዲገዛ ማስተባበሩ ይታወሳል፡፡

በሀበነዮም ሲሳይ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!