የሀገር ውስጥ ዜና

ህወሓት እስካሁን 22 የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን መግደሉ ተገለጸ

By Meseret Awoke

May 26, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 18፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) እስካሁን 22 የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር አባላትን መግደሉን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ አስታወቀ፡፡

ቡድኑ እስካሁን 20 የሚሆኑትን የአስተዳደሩ አባላትን ያገተ ሲሆን፥ አራት አባላት ጉዳት ደርሶባቸው ለሕክምና ሆስፒታል መግባታቸውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ ገልጿል፡፡ በአጠቃላይ በ46 የጊዜያዊ አስተዳደር አባላት ላይ ጥቃት መድረሱ በመግለጫው ተጠቅሷል፡፡

አሁንም ግድያ እና አፈናው በሁሉም አካባቢዎች እየቀጠለ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፥ አሸባሪው ህወሓት መኖሪያ ቤቶችን እያቃጠለ፣ መኖሪያ ቤቶችን በጥይት እየደበደበ እንደሚገኝ በመግለጫው ተጠቁሟል፡፡

ሆኖም የሀገር መከላከያ ሰራዊትና ጊዜያዊ አስተዳደሩ ክልሉን ለማረጋገትና አጥፊዎችን ለህግ ለማቅረብ በቁርጠኝነት እየሰሩ እንደሚገኙ አስታውቋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!