የሀገር ውስጥ ዜና

ሴናተር ጂም ኢንሆፍ በኢትዮጵያ የስራ ሃላፊዎች ላይ የተጣለውን የቪዛ ክልከላ ተቃወሙ

By Tibebu Kebede

May 26, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 18 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የአሜሪካዋ ኦክላሆማ ግዛት ሴናተር ጂም ኢንሆፍ ዋሽንግተን በኢትዮጵያ የስራ ሃላፊዎች ላይ የጣለችውን የቪዛ ክልከላ ተቃወሙ፡፡

ሴናተሩ ኢትዮጵያ የአሜሪካ ድጋፍ እንደሚያስፈልጋት በትዊተር ገጻቸው ባሰፈሩት ጽሁፍ አስታውቀዋል፡፡

ኢትዮጵያ አሁን ላይ የሽብር ቡድኖችን እንቅስቃሴ ለመግታት እየሰራች መሆኑን ገልጸዋል፡፡

መሰል እርምጃዎችም ሰላማዊ ውሳኔዎች ላይ ለመድረስ የሚደረገውን ጥረት የማያግዙ ናቸውም ብለዋል፡፡

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ የስራ ሃላፊዎች ላይ የቪዛ ክልከላ የሚጥል ውሳኔ ማሳለፉ ይታወሳል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!