በደቡብ ክልል ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ የሚያስተባብር ግብረ ሀይል ተቋቁሞ እየሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰላም ሚኒስቴር በደቡብ ክልል የሚገኙ ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ የሚያስተባብርና የሚመራ ግብረ ሀይል አቋቁሞ እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡፡
ግብረ ሀይሉ በጉራጌ ዞን ምስራቅ መስቃን ወረዳ በመገኘት በአካባቢው እርቅ እንዲፈጸምና ተፈናቃዮችን ወደ ቀያቸው ለመመለስ በተዘጋጀው እቅድ ላይ ከወረዳው አመራሮች ጋር በመወያየት መግባባት ላይ መድረሱ ተጠቁሟል፡፡
የወረዳው አመራር በራሱ አቅም ተፈናቃዮችን መልሶ ለማቋቋም በተለያየ አካባቢ ከሚኖሩ የአካባቢው ተወላጆች ገንዘብ በማሰባሰብ በወረዳው በቼ በልቻኖ ቀበሌ ውስጥ ለ31 አባወራ/እማወራ የመኖሪያ ቤት ግንባታ እንደተጀመረ ግብረ ሀይሉ ማረጋገጥ እንደቻለ ተገልጿል፡፡
በቀጣይም ወደ መኖሪያ ቀያቸው ለሚመለሱ ተፈናቃዮች ቦታ የመምረጥ ስራ የሚያከናውን ቴክኒካል ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ስራ እየገባ መሆኑን ከሰላም ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!