ቢዝነስ

የብሩህ የንግድና ፈጠራ ሀሳብ ውድድር 20 አሸናፊዎች ሽልማት ተበረከተላቸው

By Tibebu Kebede

May 27, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በመጀመሪያው ዙር የብሩህ የንግድና ፈጠራ ሀሳብ ውድድር አሸናፊ ለሆኑ 20 የስራ ፈጣሪዎች ሽልማት ተበረከተላቸው፡፡

የንግድና ፈጠራ ሀሳብ ውድድሩ የስራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን እና ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን ከተለያዮ አጋር አካላት ጋር በመተባበር ላለፉት ስምንት ወራት ሲካሄድ የቆየ ነው፡፡

በዚህ ውደድር ላይ 356 ተወዳዳሪዎች ለብሩህ የንግድና ፈጠራ ሀሳብ ውድድር ተመዝግበው መስፈርቱን ያሟሉ 70 የፈጠራ ባለቤቶች ሲሳተፉ ቆይተዋል፡፡

በዚህም ለውድድሩ 20 አሸናፊዎች ለእያንዳንዳቸው የ200 ሺህ ብር በአጠቃላይ 4 ሚሊየን ብር ሽልማት ተበርክቷል፡፡

እነዚህ ስራ ፈጣሪዎች በተለያዩ ዘርፎች ፈጠራዎችን ያቀረቡ ሲሆን ውድድሩ በፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ሲተላለፍ ቆይቷል፡፡ በኤፍሬም ምትኩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!