Fana: At a Speed of Life!

በምርጫው ዙሪያ ከዩኒቨርሲቲ ምሁራን፣ ከኢትዮጵያ ፕሮፌሰሮች ምክር ቤት አባላትና ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር ውይይት ተካሄደ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫን አስመልክቶ የከፍተኛ ትምህርትና ጥራት አግባብነት በሚል ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ምሁራን ከኢትዮጵያ ፕሮፌሰሮች ምክር ቤት አባላትና ከፖለቲካ ፓርቲ ተወካዮች ጋር በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የውይይት መድረኩ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴርና በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት የተካሄደ ነው፡፡
በውይይቱ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ፣ የባህርዳር ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ፍሬው ተገኝ ፣ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተወጣጡ ምሁራንና 15 የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳትፈዋል፡፡
በዚህ ወቅት ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሡ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ሣይንሣዊ ሀሣቦች እና ትንታኔዎችን በማቅረብ የዕውቀት ሽግግር ስራዎችን በመስራት ላይ ይገኛሉ ብለዋል፡፡
ምርምሮቹም ችግር ፈቺ እንዲሆኑ መሰል የውይይት መድረኮች አስፈላጊ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር ፋንታ ማንደፍሮ በኩላቸው÷ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ላይ የፖለቲካ ፓርቲዎች ያላቸውን አማራጭ ሀሣቦችን ማቅረብ ተሻጋሪ የሆነ ፖሊሲን ለመቅረፅ እንደሚረዳ ገልጸዋል፡፡
ምሁራኑም የሚገባቸውን ሚና መጫወትና አሻራቸውን ማስቀመጥ አለባቸው ብለዋል።
6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ የሚሣተፉት ሰባት የፖለቲካ ፓርቲዎችም በመድረኩ ላይ የከፍተኛ ትምህርት ጥራትና አግባብነት ላይ ያላቸውን የመከራከሪያ ነጥብ አቅርበዋል።
በሰላማዊት ተስፋዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.