Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 19፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በክልሉ የ12 ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ወስደው ከ600 በላይ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ፡፡
የማበረታቻ ሽልማት መድረኩ ” ጥራት ያለው ትምህርት በማቅረብ ብቃት ያለው ዜጋ የማፍራት ሃላፊነታችንን እንወጣ ” በሚል የተካሄደ መሆኑ ተገልጿል፡፡
በመድረኩ የክልሉ ትምህርት ቢሮ ሃላፊ አቶ ማሂ ጎዳን ጨምሮ የተለያዩ የክልል ከፍተኛ አመራሮች ፣የተሸላሚ ተማሪዎች ወላጆችና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል፡፡
በዚህ ወቅት አቶ ማሂ ጎዳ የኮሮና ቫይረስን ጫና በመጋፈጥ ለዚህ ውጤት የበቁ ተማሪዎች ፣ወላጆችና መምህራን ሊደነቁ ይገባል ብለዋል።
በ2012 ዓ.ም ከ29 ሺህ በላይ ተማሪዎች ለፈተና የተቀመጡ ሲሆን ከግማሽ በላይ የሚሆኑት 350 ና ከዚያ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውንም ሃላፊው ገልፀዋል።
በመድረኩ 600ና ከዚያ በላይ ያመጡ 130 ተማሪዎች እንዲሁም ከፍተኛ ድጋፍ ያደረጉ የተማሪ ወላጆች ተሸልመዋል፡፡
በጥላሁን ሁሴን
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.