ቢዝነስ

አየር መንገዱ በ15ኛው የጋና አፍሪካ ቢዝነስ ውድድር የወርቅ ተሸላሚ ሆነ

By Tibebu Kebede

May 27, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ አየር መንገድ በ15ኛው የጋና አፍሪካ ቢዝነስ ውድድር በማሸነፍ የወርቅ ተሸላሚ ሆነ፡፡

የአፍሪካ ሃገራትን በማስተሳሰር ያበረከተው አስተዋፅኦ ከፍተኛ በመሆኑ ነው አየር መንገዱ ተሸላሚ የሆነው፡፡

የአየር መንገዱ የአፍሪካ ሃገራትን በአቪየሽን ዘርፍ በቀዳሚነት በማገልገሉ በጋናም ኢኮኖሚ ላይ አዎንታዊ ተጽእኖ አሳርፏል ተብሏል፡፡

እንደ ጋና አቪየሽን ዘገባም 15ኛው የጋና ቢዝነስ ውድድር አህጉራዊ ነፃ የንግድ ቀጠና መተግበርን ተከትሎ በመካሄዱ ለቀጠናዊ ትብብር አስተዋፅኦ ላበረከቱ ኩባንያዎች ትኩረት ሰጥቷል፡፡

የአህጉሪቱ ትልቁ አየር መንገድ የሆነው የኢትዮጵያ አየር መንገድም የአፍሪካ ሃገራትን በኢኮኖሚ በማስተሳሰርና በኮቪድ 19 ወረርሽኝ ወቅትም የመድሃኒትና የምግብ አቅርቦት ጋናን ጨምሮ ወደ ተለያዩ ሃገራት እንዲዳረስ በማድረግ ያስመዘገበው ውጤት ለሽልማት እንዳበቃው ተገልጿል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!