ቢዝነስ

የኢትዮ-ጅቡቲ ስታንዳርድ ጌጅ አክሲዮን ማህበር ከ1 ሚሊየን ቶን በላይ ገቢና ወጪ ዕቃዎችን አጓጓዘ

By Tibebu Kebede

May 27, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 19 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ለትራንስፖርት ሚኒስቴር ተጠሪ ከሆኑት ተቋማት ውስጥ አንዱ የሆነው የኢትዮ-ጅቡቲ ስታንዳርድ ጌጅ አክሲዮን ማህበር የስራ እንቅስቃሴ በመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ተጎብኝቷል ።

የኢትዮ-ጅቡቲ ስታንዳርድ ጌጅ አክሲዮን ማህበር በዘንድሮው በጀት ዓመት 1 ነጥብ 45 ሚሊየን ቶን ገቢና ወጪ ዕቃዎች ማጓጓዙን የገለፁት ዋና ዳይሬክተሩ ኢንጂነር ጥላሁን ሳርካ በአሁኑ ወቅት ለአርሶ አደሩ ማዳበሪያ በወቅቱ እንዲደርስ ሰፊ ጥረት እያደረገ መሆኑንም አብራርተዋል።

አክሲዮን ማህበሩ ከገቢና ወጪ ማጓጓዝ አገልግሎት በተጨማሪ ድንበር ተሻጋሪ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት የኢትዮጵያ እና ጀቡቲን ህዝብ ማስተሳሰሩን የትራንስፖርት ሚኒስቴር መረጃ ያመላክታል፡፡

በኮቪድ-19 ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የህዝብ ትራንስፖርት በመጀመሩ በቀን በአማካይ 400 ሰዎችን እያመላለሰ መሆኑንም የአክሲዮን ማህበሩ ዋና ዳይሬክተር አስታውቀዋል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!