ስፓርት

ኢትዮጵያ ቡና በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳታፊ መሆኑን አረጋገጠ

By Tibebu Kebede

May 28, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በቤት ኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ኢትዮጵያ ቡና ከአዳማ ከተማ አቻ ተለያዩ፡፡

ረፋድ ላይ የተካሄደው ጨዋታ አንድ አቻ በሆነ ውጤት ተጠናቋል፡፡

አዳማ ከተማ በበላይ አባይነህ ጎል ጨዋታውን መምራት ቢችልም አበበ ጥላሁን ለቡናማዎቹ የአቻነቷን ጎል አስቆጥሯል፡፡

ውጤቱን ተከትሎም ኢትዮጵያ ቡና 41 ነጥብ በመያዝ የአፍሪካ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ተሳትፎ ማረጋገጡን የሶከር ኢትዮጵያ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!