Fana: At a Speed of Life!

በደቡብ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ተምች ተከሰተ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 20 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በደቡብ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ሁለት አይነት ተምች መከሰቱ ተገለፀ፡፡
ማህበረሰቡ የተከሰተውን ተምች የመከላከል ስራውን እንዲያጠናክር የክልሉ እርሻና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ቢሮ ጥሪ አቅርቧል፡፡
የቢሮው ምክትል ሀላፊ አቶ ዳንኤል አዳምጠው አዲሱ መጤ ተምች የተሰኘው የመጀመሪያው የተምች አይነት በቆሎ ላይ ከፍተኛ አደጋ ሊያደርስ የሚችል ነው ያሉ ሲሆን ሁለተኛው የተምች አይነት ደግሞ የአፍሪካ አርሚ ወርም የተሰኘውና ሁሉንም ሰብሎች ሊያጠቃ የሚችል ነው ብለዋል፡፡
ከፍተኛ ርብርብ ተደርጎ መቅረፍ ካልተቻለም ጉዳቱ ሰፊ ሊሆን ይችላል ብለዋል።
በአሁኑ ሰዓት ተምቹ በ34 ሺህ ሔክታር ላይ የተከሰተ ሲሆን ከዚያ ውስጥ 18 ሺህ ያህል ሔክታር መሬትን መቆጣጠር እንደተቻለ ተናግረዋል ።
የወላይታ የጋሞ ዞኖችን ጨምሮ በሰባት ዞኖች ውስጥና በአንድ ልዩ ወረዳ መከሰቱ የተነገረለት ተምች መከላከል ካልተቻለ ወደ ሌሎች አካባቢዎች ሊስፋፋ እንደሚችልም ተነግሯል፡፡
ቢሮው ችግሩን ለመቅረፍ ኬሚካል የማቅረብ ስራዎች በማከናወን ላይ ቢሆንም በባህላዊ መንገድ የሚደረገው የመከላከል ተግባር የሚበረታታ ነው ሲሉ ተናግረዋል ።
በብርሃኑ በጋሻው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.