የሀገር ውስጥ ዜና

ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ 122 የህክምና ዶክተሮችን አስመረቀ

By Tibebu Kebede

May 29, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 21 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ የሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ያስተማራቸውን 122 የህክምና ዶክተሮች አስመረቀ፡፡

የጤና ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ደረጀ ዱጉማ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲው በጤናው ዘርፍ ብቁና ተወዳዳሪ ተማሪዎችን እያፈራ ይገኛል፡፡

ይህም የዩኒቨርሲቲውን ተሞክሮ ያሳያል ማለታቸውን የአማራ ሚዲያ ኮርፖሬሽን ዘገባ ያመላክታል።

ዩኒቨርሲቲው የማኅበረሰብ አገልግሎት በመስጠት እንደሚታወቅ ያነሱት ሚኒስትር ዲኤታው፥ የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል ያደረገው ጥረት አንዱ ማሳያ መሆኑንም ገልጸዋል።

ተመራቂዎች በሥራ ዓለም የተለያዩ ፈተናዎች እንደሚያጋጥማቸው አውቀው ከወዲሁ ራሳቸውን ማዘጋጀት እንዳለባቸውም አስገንዝበዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!