Fana: At a Speed of Life!

የፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ነፃ የአየር ሰአት ድልድል ለ12 ቀናት ተራዘመ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 21፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የ6ኛው ሃገር አቀፍ ምርጫ የድምፅ መስጫ ቀን መራዘሙን ተከተሎ የፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ነፃ የመገናኛ ብዙኃን የአየር ሰአት ድልድል ለተጨማሪ 12 ቀናት ተራዝሟል፡፡

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በምርጫ መራዘም ምክንያት ለፖለቲካ ፓርቲዎች የመደበውን ተጨማሪ የአየር ሰዓት ይፋ አድርጓል፡፡

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን በጋራ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ ፓርቲዎች ተጨማሪ የአየር ሰአታቸውን ተጠቅመው ከግንቦት 24 እስከ ሰኔ 9 ድረስ መቀስቀስ እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡

የድምፅ መስጫ ቀን አራት ቀን እስኪቀረው ድረስ የምርጫ ቅስቀሳ ዘመቻ የሚካሄድ ሲሆን፥ አራቱ ቀናቶች የፅሞናን ጊዜ ታሳቢ ያደረጉ ናቸው ተብሏል፡፡

በአዲስ ሙሉነህ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.