የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ በማዘመን አምራች ዜጋን ለመፍጠር እየተሰራ ነው
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) ትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ በማዘመን አምራች ዜጋን ለመፍጠር ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን አስታወቀ፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ሚኒስቴሩ የትምህርት ዘርፉን በቴክኖሎጂ ለማዘመን የተለያዩ ስራዎችን እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በቀጣይም ቴክኖሎጂን መሰረት ያደረጉ የመማር ማስተማር ሂደቶችን ተግባራዊ እንደሚያደርግ ገልፀዋል፡፡
በአሁን ሰዓት ትምህርትን በቴክኖሎጂ ለማዘመን በሚደረገው ሂደት ውስጥ ለ ሁለተኛ ደረጃ የትምህርት እርከን ትኩረት መሰጠቱን የገለፁት ሚኒስትሩ ይህም ወጣቶች በቴክኖሎጂ በመታገዝ አምራች ዜጋ እንዲሆኑ ለማድረግ መሆኑን ተናግረዋል።
በዚህ እንቅስቃሴ የሀብት እጥረት ትልቅ ችግር እንደሆነና ችግሩን ለመፍታትም መንግስት አጋር ድርጅቶችን በማስተባበር ሀብት የማሰባበሰብ ስራ እየተሰራ መሆኑን መግለፃቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!