Fana: At a Speed of Life!

የዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን በኢትዮጵያ ለ29ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የዓለም ትምባሆ የማይጨስበት ቀን በኢትዮጵያ ለ29ኛ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ34ኛ ጊዜ እየተከበረ ነው፡፡
ቀኑ “ትምባሆ ያጨሳሉ? እንግዲያውስ ለማቆም ቆራጥ ይሁኑ” በሚል መሪ ቃል ነው እየተከበረ የሚገኘው፡፡
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ ቀኑን አስመልክተው ትምባሆ እንደ የልብ ፣ ካንሠር፣ የመተንፈሻ አካላት በሽታ እና የስኳር ህመም ላሉ ተላላፊ ያልሆኑ በሽታዎች ተጋላጭነትን የሚጨምር መሆኑን ገልፀዋል፡፡
እንዲሁም ትምባሆ አጫሾች በኮቪድ 19 ወረርሽኝ፣ ለጽኑ ህመምና ለሞት የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ መሆኑን አሳይቷል ብለዋል ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገፃቸው፡፡
በሌላ በኩል ቀኑን በማስመልከት ትምባሆ ማጨስን በማቆም ተላላፊ ካልሆኑ ህመሞችና ከኮቪድ19 የከፋ ህመምና ሞት ራሳችንን እንከላከል !፣ትምባሆ ማጨስ ማቆም ጤናማና ደስተኛ ያደርጋል! የሚሉ እና ሌሎች መልዕክቶች እየተላለፉ ነው፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.