Fana: At a Speed of Life!

የሥራ ዕድል ፈጠራ የፖሊሲ አማካሪ ምክር ቤት በሦስት ዘርፎች ያጠናቸውን ጥናቶች ለምክረ ኃሳብ ውይይት አቀረበ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 23፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የሥራ ዕድል ፈጠራ የፖሊሲ አማካሪ ምክር ቤት በሦስት ዘርፎች ያጠናቸውን ጥናቶች ለምክረኃሳብ ውይይት አቀረበ፡፡
የሥራ ዕድል ፈጠራ የፖሊሲ አማካሪ ምክርቤት በ10 ዓመት የሥራ ዕድል ፈጠራ መሪ ዕቅዱ መሰረት ተቋቁሞ የሥራ ዕድል ፈጠራን የሚመለከቱ የሕግ ማዕቀፎችና አሠራር ሥርዓቶች ዙሪያ ያሉትን ክፍተቶች ለማሟላት የሚያስችሉ የፖሊሲ ምክረ ሐሳብ ሥራዎችን በመሥራት ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
ምክር ቤቱ ከልዩ ልዩ ዘርፎች፣ የጥናትና ምርምር ተቋማትና የግሉ ዘርፍ ምሁራን የተካተቱበት ሲሆን ፖሊሲዎች ለሥራ ዕድል ፈጠራ ምቹ እንዲሆኑና ዕቅዶችም በጥናትና ምርምር ላይ የተመሠረቱ እንዲሆኑ የሚያስችሉ ግብዓቶችን የሚሰጥ ነው ተብሏል።
በምክር ቤቱ ሶስተኛ የምክክር መድረክ አማራጭ የኃይል ልማትና አቅርቦትን በማስፋፋትና ምርታማነትን በማሳደግ ሰፊና ዘላቂ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር የሚያስችል ተተግባሪ ፖሊሲና ስትራቴጂ ፣ የግብርና ምርትን በማጠናከር አካታችና ዘላቂ የሥራ ዕድሎች መፍጠር ስለሚቻልበት ሁኔታ እንዲሁም ቆዳና ከቆዳ ጋር የተያያዙ ምርቶችን እሴት ሰንሰለትን በማጠናከር ምርታማነት ለመጨመርና ከሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች ጋር ያለውን መስተጋብር በማሳደግ የሥራ ዕድል መፍጠር የሚቻልበትን ነባራዊ ሁኔታ ያገናዘቡ የፖሊሲ ምክረ ሐሳቦች ቀርበዋል።
በመድረኩ የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ንጉሡ ጥላሁን በበጀት ዓመቱ እንደ ሃገር የታቀዱ የሥራ ዕድሎችን ለመፍጠር በሚደረገው ርብርብ ውስጥ ቁልፍ የፖሊሲና ስትራቴጂ ማነቆዎችን ለመፍታት የሚያስችሉ ጥናቶችን መሥራት በተለይም ፖሊሲዎችን ሥራ ተኮር ማድረግ አማራጭ መሆኑን መግለፃቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.