የሀገር ውስጥ ዜና

በብልጽግና ፓርቲ ስብሰባ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተባለ በማስመሰል የተለቀቀው የድምፅ ፋይል በውሸት የተቀነባበረ ነው – ጠ/ሚ ጽህፈት ቤት

By Tibebu Kebede

May 31, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 23 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ባለፈው ሳምንት በብልጽግና ፓርቲ ስብሰባ ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትሩ የተባለ በማስመሰል የተለቀቀው የድምፅ ፋይል በውሸት የተቀነባበረና ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተለያያየ ጊዜ የተናገሩትን በመቁረጥና በመቀጠል የተፈጠረ የሀሰት መረጃ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ጽህፈት ቤቱ በዚህ የሀሰት መረጃ ዘመን እና ምርጫው እየተቃረበ ባለበት ወቅት ዜጎች፥ አለመግባባትን ለመፍጠር ባተኮሩ መሰል የማሳሳት የመረጃ ዘመቻ እንዳይታለሉም መልዕክት አስተላልፏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!