‘‘አንድ ድምፅ አንድ አቋም ለታላቁ ህዳሴ ግድብ እውን መሆን ’’ በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ ተካሄደ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ከታላቁ ህዳሴ ግድብ ህዝብ ተሳትፎ ማስተባበሪያ ምክር ቤት ጋር በመተባበር አንድ ድምፅ አንድ አቋም ለታላቁ ህዳሴ ግድብ እውን መሆን በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ በአርባ ምንጭ ተካሂዷል፡፡
በመድረኩ ላይ የውሃ መስኖና ኢነርጂ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፣ የታላቁ ህዳሴ ግድብ ማስተባባሪያ ምክር ቤት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አረጋዊ በርሄን ጨምሮ የተለያዩ የፌዴራል እና የክልል ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የውሃ ሀብት ተመራማሪዎችና ምሁራን ተገኝተዋል።
ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ አጭር ማብራሪያ ያቀረቡት ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ፥ የትኛውንም የውስጥ እና የውጭ ተፅዕኖ በመቋቋም የህዳሴ ግድቡን ከስኬት ማድረስ ይኖርብናል ብለዋል።
ከድርድር ሂደቱ ጋር በተገናኘ የውሃው ባለቤት የሆነችውን ኢትዮጵያ አግላይ የሆነ ስምምነት ተቀባይነት ስለሌለው በተፋሰስ ሀገራት በኩል የሚመጣው ጥያቄ በፍፁም ተቀባይነት የለውምም ነው ያሉት።
የአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዳምጠው ዳርዛ በበኩላቸው፥ ለህዳሴው ግድብ ስኬት የሁሉም ርብርብ አስፈላጊ ስለሆነ በአንድ ድምፅ በአንድ አቋም መሰለፍ እንደሚገባ አንስተዋል።
በመድረኩ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል።
በጥላሁን ሁሴን እና ኢብራሂም ባዲ
ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!