Fana: At a Speed of Life!

ሁሉም ኢትዮጵያዊ በጋራ በመቆም ለሀገሩ ድጋፍ ማድረግ አለበት–በካናዳ የሚኖሩ ኢትዮ -ካናዳዊያን

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)ኢትዮ – ካናዳውያን የአሜሪካ መንግስት በኢትዮጵያ ላይ የጣለውን የጉዞና ተያያዥ ማዕቀብ በመቃወም በካልጋሪ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።
ትውልደ ኢትዮጵያዊያኑ በትግራይ ክልል የህወሃት አሸባሪ ቡድን በሰሜን ዕዝ የመከላከያ ሰራዊታ ላይ ያደረሰውን ኢሰብዓዊ ጭፍጨፋ ተከትሎ መንግስት የወሰደውን የህግ ማስከበርና ወንጀለኞቹን ለህግ የማቅረብ ህጋዊ እርምጃ እንደሚደግፉ ገልጸዋል።
ሆኖም ይህን ክስተት ተከትሎ የአሜሪካ መንግስት እውነታውን በትክክል ሳይመረምር በተሳሳተና እውነትን መሰረት ባላደረግ ሁኔታ የኢትዮጵያን መንግስት ከአሸባሪዎች እኩል በመመልከት ማዕቀብ መጣሉ ስህተት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
ሰልፈኞቹ በመልዕክታቸው ወቅቱ ኢትዮጵያ ከምንጊዜውም በላይ የዜጎቿን ድጋፍ የምትፈልግበት ጊዜ መሆኑን፣ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ያለምንም የሀይማኖት፣ የብሔርና የፆታ ልዩነት በአንድነት በመቆም ድጋፉን ማድረግ አለባቸው ነው ያሉት።
አሜሪካም ሆኑ ሌሎች ምዕራባውያን አገሮች በኢትዮጵያ ላይ ተጽዕኖ ለማድረግ የሚፈልጉት ሀገሪቱ ደሃ በመሆኗ መሆኑን ገልጸው፣ መንግስት ሀገሪቷን ከድህነት ለማውጣት የሚያደርገውን ጥረት በተለያየ መንገድ እንደሚደግፉና ተናግረዋል።
ወደ ኢትዮጵያ የሚልኩትን ገንዘብ በህጋዊ መንገድ ብቻ እንደሚልኩ፣ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ በተያዘለበት ጊዜ መሰረት ሙሌቱ እንዲካሄድና ፕሮጄክቱም እንዲጠናቀቅ የሚያደርጉትን ድጋፍ አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል።
በተመሳሳይ የካናዳ መንግስትም በኢትዮጵያ የተጀመረው ለውጥ መሰረት እንዲይዝ እንዲደግፍና አላስፈላጊ ጫና ኢትዮጵያ ላይ ከማሳረፍ እንዲቆጠብ መጠየቃቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.