Fana: At a Speed of Life!

በጎንደር በሰላምና አብሮነት ዙሪያ ውይይት ተጀመረ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ በሰላም፣ በአብሮነት፣ በሃይማኖትና በብሄር ብዝሃነት ላይ የሚመክር ውይይት በጎንደር ከተማ እያካሄደ ነው።
የኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባኤ ምክትል ጠቅላይ ፀሐፊ ሃጂ መስዑድ አደም፥ “ኢትዮጵያ የተጋረጠባትን አደጋ ለመቀልበስ የሃይማኖት አባቶች ለሰላም መስፈንና መረጋገጥ አጥብቀን ልንሰራ ይገባል” ብለዋል።
ጉባኤው በህዝቦችና ሃይማኖቶች መካከል ለዘመናት የዘለቀውን የመከባበርና የመተባበር አኩሪ ባህል ይበልጥ ለማጠናከር የተለያዩ ስራዎች እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።
በምክክር መድረኩ የግጭት አያያዝና አፈታት፣ የግጭት ቅድመ ማስጠንቀቂያና ምላሽ ሂደት እንዲሁም የሃይማኖትና የብሄር ብዝሃነት አያያዝ በሚል ርዕስ በምሁራን ጥናታዊ ፅሁፎች ቀርበው ምክክር እንደሚደረግ ተመላክቷል።
ለሁለት ቀን በሚቆየው የምክክር መድረክ ከባህርዳር፣ ጎንደርና አካባቢው የተውጣጡ የሃይማኖት መሪዎች፣ የሃገር ሽማግሌዎች፣ ታዋቂ ግለሰቦች፣ የመንግስት የስራ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ እንደሚገኙ ኢዜአ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.