የሀገር ውስጥ ዜና

ለፌዴራል እና ለክልል ኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ነው

By Tibebu Kebede

June 01, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 24 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት የፕሬስ ሴክሬታሪያት ለፌዴራል እና ለክልል ኮሙዩኒኬሽን ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡

ስልጠናው ‘ተግባቦት በዲጂታል ዘመን’ እና ‘የቀውስ ተግባቦት’ በሚል ርዕስ እየተካሄደ መሆኑን የጽህፈት ቤቱ መረጃ ያመላክታል፡፡

ይህ ስልጠና በኮሙዩኒኬተሮች መካከል ጠንካራ ትስስር በመፍጠር ብሄራዊ የግንኙነት ሥነ-ምህዳሩን ለማጠናከር ከሚደረጉ ጥረቶች አንዱ አካል ነው ተብሏል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!