የ10 ሀገራት አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች ለፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሹመት ደብዳቤያቸውን አቀረቡ
አዲስ አበባ፣ ግንቦት 24፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) የ10 ሀገራት አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮች ለፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ የሹመት ደብዳቤያቸውን በዛሬው ዕለት አቅርበዋል፡፡
ለፕሬዘዳንቷ የሹመት ደብዳቤያቸውን ያቀረቡት የካናዳ፣ የእስራኤል፣ የባንግላዴሽ፣ የሞዛምቢክ፣ የናይጄሪያ፣ የሶማሊያ፣ የቤኒን፣ የኢስቶኒያ፣ የቬትናም እና የቤላሩስ አምባሳደሮች ናቸው።
እንደ ኢቢሲ ዘገባ አዲስ ተሿሚ አምባሳደሮቹ ከፕሬዝዳንቷ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሀገራቱ ከኢትዮጵያ ጋር ያላቸውን ሁሉን አቀፍ ግንኙነት ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገልፀዋል፡፡
ፕሬዚዳንቷ በበኩላቸው አምባሳደሮቹ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው የሥራ ቆይታ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግላቸው መናገራቸውን ውይይቱን የተከታተሉት አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!