Fana: At a Speed of Life!

የትግራይ ክልል አርሶ አደሮች 20 ትራክተሮችን በድጋፍ ሊያገኙ ነው

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የ ዩ ኤስ አይድ ድጋፍ የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት (USID) ከማረት ጋር በመተባበር በትግራይ ክልል ለሚገኙ አርሶ አደሮች የሚውሉ 20 ትራክተሮችን ለመደገፍ በዝግጅት ላየ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ትራክተሮቹ በክልሉ ላጋጠመ ችግር የመፍትሄ አካል መሆናቸውን የገለጹት የማረት የኑሮ ማሻሻያ ዘርፍ ከፍተኛ ባለሞያ አቶ ረዘነ ገብሩ፤ እያንዳንዳቸው በ1 ነጥብ 2 ሚልዮን የተገዙ ሲሆን ባጣቃላይ በ30 ሚልዮን ብር ወጪ የተገዙ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

በትግራይ ክልል ለትራክተር ሞቹ የሆነ መልክኣ ምድራዊ አቀማመጥ ያላቸው 6 ወረዳዎች የሚከፋፈሉ ሲሆኑ ለያንዳንዳቸው 3 ኦፕሬተሮች በመቅጠር ማረት ሙሉ ወጪያቸውን በመሸፈን ከ14 ሺ 8መቶ አርሶ አደሮች በላይ ተጠቃሚ እንደሚያደርጉም አቶ ረዘነ ገብሩ ገልፀዋል፡፡

ከቀጣይ ሐሙስ ጀምረው ወደ ወረዳዎቹ እንደሚከፋፈሉ የተነገረ ሲሆን ህዝቡም የንብረቱ ባለቤት በመሆኑ አስፈላጊ ጥበቃ እንዲያደርግላቸውን አቶ ረዘነ መልእክት ማስተላለፋቸውን የትግራይ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.