Fana: At a Speed of Life!

የምሰራቅ አማራ የሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎችና የምርምር ማዕከላት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የምሰራቅ አማራ ዩኒቨርሲቲዎችና በቀጠናው የሚገኙ የምርምር ማዕከላት በጋራ ለመስራት የስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ።

የስምምነት ሰነዱ በህብረት በመስራት መሬት የነካ ጥናትና ምርምር እንዲሁም የማህበረሰብ አገልግሎቶችን በማጠናከር አብሮ ለመስራት የሚያስችል ነው፡፡

በመቅደላ አምባ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ምስራቅ አማራ የሚገኙ የወልድያ ፣ ወሎ ፣የሲሪቃ ግብርና ምርምር ማዕከል ፣የደሴ የእጽዋት ዘርና ሌሎች የግብርና ግብአቶች ቁጥጥር ኳራንታይን ማዕከል ፣የሰሜን ወሎ ፣ደቡብ ወሎ እና ኦሮሚያ ልዩ ዞኖችን ያካተተ ‹‹ ህብረት ለዘላቂ ልማት ›› በሚል መሪ ቃል በቅንጅት ለመስራት የሚያስችል የጋራ የስምምነት ሰነድ ተፈራርመዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲዎቹ እና የምርምር ማዕከላቱ የሰብል ፣የእንስሳት እና የአትክልትና ፍራፍሬ ምርት የሚገኝባቸው አከባቢ እንደመገኘታቸው የማህበረሰቡን ምርታማነት የሚያሳድጉ እና አካባቢውን የሚቀይሩ ጉዳዮች ላይ ትኩረት በማድረግ ሊሰሩ ይገባል ተብሏል፡፡

ምንጭ፡-የመቅደላ አምባ ዩኒቨርስቲ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.