የሀገር ውስጥ ዜና

በመዲናዋ 500 ሺህ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

By Tibebu Kebede

June 02, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በአዲስ አበባ ከተማ በአምስት አመታት ውስጥ 500 ሺህ የጋራ መኖሪያ ቤቶችን መገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ፡፡

ስምምነቱን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ እና ፕሮፐርቲ 2000 ደቡብ አፍሪካ ኩባንያ ተወካይ ተፈራርመውታል፡፡

ለግንባታው 4 ነጥብ 2 ቢሊየን ዶላር ወጪ የሚደረግ ሲሆን፥ ሙሉ ወጪው በኩባንያው ይሸፈናል ተብሏል፡፡

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደርም ለግንባታ የሚያስፈልገውን መሬት ያቀርባል ነው የተባለው፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በ30 አመታት ክፍያ ለተጠቃሚዎች የሚቀርቡ ሲሆን፥ የተቀናጀ የመንግስትና የግሉ ዘርፍ ትብብር አካል መሆኑ ተገልጿል፡፡

የጋራ መኖሪያ ቤቶቹ በ1 በመቶ አነስተኛ ወለድ የሚቀርቡ ሲሆን፥ በቀጣዮቹ አምስት አመታት ውስጥም 500 ሺህ ቤቶች እንደሚገነቡም ነው የተገለጸው፡፡

ለመኖሪያ ቤቶቹ በመሃል ከተማ የመልሶ ማልማት በሚከናወንባቸው እና በአይሲቲ ፓርክ አካባቢ ቦታ መለየቱም በስምምነቱ ወቅት ተነስቷል፡፡

በሃይለኢየሱስ ስዩም

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!