Fana: At a Speed of Life!

በምስራቅ ጎጃም ዞን በበጀት ዓመቱ ከጎብኚዎች ከ74 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ ተገኘ

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 25፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን እነብሴ ሳር ምድር ወረዳ በዚህ በጀት አመት የመስህብ ስፍራዎችን ከጎበኙ ጎብኚዎች ከ74 ሚሊየን ብር በላይ ገቢ መገኘቱን የወረዳው ባህልና ቱሪዝም ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በጽህፈት ቤቱ የቱሪዝም መዳረሻ ልማት ባለሙያ ወይዘሮ የሺሃረግ ጸጋ እንዳሉት፥ በወረዳው ያሉ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የተሻለ አገልግሎት እንዲሰጡ የክትትልና ቁጥጥር ስራው ተጠናክሮ መሰራቱ ለወጣቶች የስራ ዕድል ፈጠራ ምቹ ሆኗል ብለዋል፡፡

በወረዳው ያለው የጎብኚዎች ፍሰት እንዲጨምር ሁሉም አገልግሎት ሰጭ ተቋማት ሰፊ የስራ እድል ፈጠራ ስራ በመስራታቸው ተቋማቱ ምቹና ቀልጣፋ አገልግሎት እየሰጡ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በበጀት አመቱ የመርጡለማርያም ገዳም፣ የአብርሐ ወአፅብሐ ፍርስራሽን ጨምሮ ሌሎች የመስህብ ሀብቶችን ይጎበኛሉ ተብለው በእቅድ ከተያዙት 29 ሺህ 276 ጎብኚዎች መካከል እስካሁን 37 ሺህ 300 ጎብኚዎች መጎብኘታቸውንና ከ74 ሚሊየን 400 ሺህ ብር በላይ ገቢ መገኘቱን ጠቁመዋል፡፡

በወረዳው ባሉ የመስህብ ስፍራዎች አካባቢ የመሰረተ ልማት አለመሟላት ለጎብኚዎች ፍሰት እንቅፋት በመሆኑ ትኩረት ሊሰጠው እንደሚገባ ወይዘሮ የሺሃረግ ጠይቀዋል፡፡

በሰላም አሰፋ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.