Fana: At a Speed of Life!

በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየው የአዘዞ ጎንደር መንገድ አስፓልት የማልበስ ስራ ተጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 25 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ)በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየው የአዘዞ ጎንደር መንገድ አስፓልት የማልበስ ስራ ተጀመረ።

የአስፓልት ማልበስ ስራውን የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘሁ ተሻገር በስፍራው ተገኝተው ተመልክተዋል፡፡

በተለያዩ ምክንያቶች የዘገየውን ይህን ፕሮጀክት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ መሆኑን  የጎንደር ከተማ ከንቲባ ሞላ መልካሙ ተናግረዋል።

መጠናቀቅ ከነበረበት ጊዜ አንፃር የመንገድ ስራው ዘግይቷል ያሉት ከንቲባው አቶ ሞላ መልካሙ፥ ከመንገዱ ጋር በተያያዘ ያሉት የሶስተኛ ወገን ችግሮች በመፈታታቸው ፕሮጀክቱ ለውጥ አሳይቷል ብለዋል።

ከመነሻው እስከ አንድ ነጥብ ስምንት ኪሎ ሜትር አስፓልት የማልበስ ስራ የተጀመረ ሲሆን እስከ ስድስት ነጥብ አምስት ኪሎሜትር ያለውን የመንገዱ ክፍል ሙሉ በሙሉ አስፓልት የማልበስ ስራው ይከናወናል ተብሏል።

የፕሮጀክቱ አፈፃፀም 52 በመቶ ደርሷል ያሉት የሀምዳ ኢንጅነሪንግ ኮንሰልት ፕሬዚዳንት ኢንጂነር ኩምሳ ገለታ የመንገድ ስራውን በፍጥነት ለማጠናቀቅ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

የመንገድ ስራው በጥሩ ሁኔታ ላይ መሆኑን የገለፁት አቶ ኩምሳ አስፓልት የማልበስ ስራው በ27 ቀናት ይጠናቀቃል ብለዋል።

የስሚንቶ  አቅርቦት ዕጥረት እና ወሰን የማስከበር ችግሮች እንዲፈቱላቸው የጠየቁት አቶ  ኩምሳ ገለታ በክረምት ጊዜውን ለመስራት ዝግጁ ነን ብለዋል።

የከተማ አስተዳደሩ በበኩሉ ችግሮችን በፍጥነት እፈታለሁ ብላል።

የአዘዞ ጎንደር 12 ነጥብ 6 ኪሎ ሜትር አስፓልት መንገድ ስራ በ2010 ዓ.ም 871 ሚሊየን ብር በጀት ተመድቦለት በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የተጀመረ ፕሮጀክት ነው።

በተያያዘም ርዕሰ መስተዳድሩ የጎንደር ከተማ የመጠጥ ውሃ ምንጭ የሆነውን የአንገረብ ግድብ በደለል መሞላት ተከትሎ የሚደረገውን ደለል የማውጣት ስራ ተመልክተው ስራውን አበረታቷዋል።

በልማት ፕሮጀክቶቹ አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴ ላይ አበረታች ለውጥ መኖሩን አቶ አገኘሁ ተናግረዋል።

በምናለ አየነው

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.