የሀገር ውስጥ ዜና

በቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው የተገነባው ኢፋ ቢሊቃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

By Tibebu Kebede

June 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው በኦሮሚያ ክልል ሀዊ ጉዲና ወረዳ በፅህፈት ቤታቸው ያስገነቡትን ኢፋ ቢሊቃ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አስመረቁ፡፡

ትምህርት ቤቱ 13 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወጪ ተደርጎበታል፡፡

በሁለት ፈረቃ 1 ሺህ 800 ተማሪዎችን ተቀብሎ የሚያስተናግድ ሲሆን፥ የቤተ ሙከራ፣ የመማሪያ ክፍሎች፣ ቤተ መጽሐፍት እና የኮምፒውተር ላቦራቶሪን ያካተተ ነው ተብሏል።

ወይዘሮ ዝናሽ በዚህ ወቅት ባስተላለፉት መልዕክት ፅህፈት ቤቱ በሁሉም ክልሎች ያስገነባቸውን ትምሀርት ቤቶች መምህራን፣ተማሪዎች እንዲሁም የአካባቢው ማህበረሰብ ጥበቃ እና እንክብካቤ እንዲያደርጉላቸው እንዲሁም ለተሰራበት ዓላማ ብቻ እንዲውል ጥሪ አቅርበዋል፡፡

የሃዊ ጉዲና ዳሮ ቢሊቃ ቀበሌ ነዋሪዎችም ልጃቸውን ወደ ትምህርት ቤት ልከው እንዲያስተምሩ አደራ ብለዋል፡፡

በምርቃት ስነ ስርአቱ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸውን ጨምሮ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳና ሌሎች የክልሉ የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

በፈትያ አብደላ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!