ስፓርት

ፋሲል ከነማ ከሂውማን ብሪጅ ኢትዮጵያ ጋር የትጥቅ አቅርቦት ስምምነት ተፈራረመ

By Tibebu Kebede

June 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ከሂውማን ብሪጅ ኢትዮጵያ ጋር የትጥቅ አቅርቦት ስምምነት አደረገ።

በስምምነቱ መሰረት ሂውማን ብሪጅ ኢትዮጵያ ለፋሲል ከነማ ከ5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የመጫዎቻ ጫማ፣ ኳስ፣ ማሊያዎችና የማሰልጠኛ ቁሳቁሶች በድጋፍ መልክ እንደሚሰጥ ከክለቡ የፌስ ቡክ ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ስምምነቱ የድርጅቱ ዳይሬክተር ተወካይ አቶ ለማ አታክልቲ እና የክለቡ ስራ አስኪያጅ አቶ አብዮት ብርሃኑ በተገኙበት ተከናውኗል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!