የሀገር ውስጥ ዜና

በ34 ሚሊየን ብር የተገነባው የጉርሱም ሆስፒታል ስራ ጀመረ

By Tibebu Kebede

June 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በ34 ሚሊየን ብር የተገነባው የጉርሱም ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ተመርቆ ስራ ጀመረ።

ሆስፒታሉ የጤና አገልግሎትን አስመልክቶ ከዚህ ቀደም በአካባቢው ነዋሪዎች ሲቀርብ የነበረውን ቅሬታ እንደሚፈታ ታምኖበታል።

በኦሮሚያ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድር ወይዘሮ ጫልቱ ሳኒ የሚመራው ልዑክ የጉርሱም ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልን መርቆ ስራ አስጀምሯል።

መንግስት ለጤናው ዘርፍ ልዩ ትኩረት ሰጥቶት እየሰራ ነው ያሉት ምክትል ርዕሰ መስተዳድሯ፥ ዘርፉ የሚጠይቀውን አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ያስችል ዘንድ እንደ ጉርሱም ወረዳ ያሉ ሆስፒታሎች ወደ ስራ መግባታቸው አስፈላጊ ነው ብለዋል።

በነስሪ የሱፍ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!