Fana: At a Speed of Life!

በልደታ ክፍለ ከተማ በየቀኑ ከ800 በላይ ዜጎችን መመገብ የሚችል ማዕከል ስራ ጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነባው አራተኛው የተስፋ ብርሃን የምገባ ማዕከል ተመርቆ ስራ ጀመረ፡፡

ከቆሻሻ ገንዳ ምግብ ለቅመው ከመመገብ በቀን አንድ ጊዜ እንኳን መመገብ እስከማይችሉት የከፋ ችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን ለመመገብ የምገባ ማዕከላት መቋቋማቸውን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤ ተናግረዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ መንግስታዊ እና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማትን በማስተባበር 5 የምገባ ማዕከላትን በመገንባት ዜጎችን ለመመገብ እየተንቀሳቀሰ ይገኛል፡፡

በልደታ ክፍለ ከተማ የተገነባው የምገባ ማዕከል ከአዋሽ ባንክ ጋር በመተባበር የተገነባ ሲሆን በምግብ አቅርቦቱ በኩል የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ትብብር አድርጓል፡፡

በችግር ውስጥ ያሉ ወገኖችን ከመመገብ ጎን ለጎን ሰርተው መለወጥ ለሚችሉ ወገኖችን ስራ በመፍጠር ሰልጥነው ወደ ስራ እንዲሰማሩ ይደረጋል መባሉንም የአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ ዘገባ ያመላክታል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.