የሀገር ውስጥ ዜና

በ39 ሚሊየን ብር የተገነባው የሮቤ ኢፈ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ

By Tibebu Kebede

June 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) በኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት በኢፈ ቦሩ ፕሮጄክት ስር የተገነባው የሮቤ ኢፈ ቦሩ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተመረቀ፡፡

በትምህርት ቤቱ የምርቃት ስነ ስርዓት ላይ ቀዳማዊት እመቤት ዝናሽ ታያቸው፣ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ርዕሰ መስተዳድር አቶ ሽመልስ አብዲሳ፣ የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ቶላ በሪሶ እና ሌሎች የክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች መገኘታቸውን ኦቢኤን ዘግቧል፡፡

ለትምህርት ቤቱ ግንባታ 39 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን፥ ከፍተኛ ውጤት ያመጡ 700 ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተናግዳል ተብሏል፡፡

መማሪያ ክፍሎችን ጨምሮ ቤተ መጽሐፍት፣ ቤተ ሙከራ እና የኮምፒውተር ላቦራቶሪዎችን ያካተተ ነው፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!