Fana: At a Speed of Life!

የአፍሪካ ተምች በጅማ ዞን ስምንት ወረዳዎች ተከሰተ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአፍሪካ ተምች በጅማ ዞን ስምንት ወረዳዎች መከሰቱን የጅማ እፅዋት ክሊኒክ ማዕከል አስታወቀ፡፡
የማዕከሉ ሀላፊ አቶ ቦና ሂርጳ እንደገለፁት÷ ተምቹ በስምንት ወረዳዎች 52 ቀበሌዎችን አዳርሷል፡፡
ይህ ተምች በ6 ሺህ 476 ነጥብ 75 ሄክታር መሬት ላይ በሚገኝ የበቆሎ፣ ማሽላ፣ ቦሎቄ፣ ዳጉሳ፣ ለውዝ እና የግጦሽ መሬት ላይ መከሰቱን ተገልጿል፡፡
ተምቹን ለመከላከል ከኬሚካል ይልቅ ባህላዊ ዘዴ ተመራጭ በመሆኑ አርሶ አደሩ ማሳውን በየጊዜው እየፈተሸ የመከላከል ስራውን አጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባ ሃላፊው አሳስበዋል፡፡
ተምቹ በዞኑ በዚህ ዓመት ለመጀመሪያ ጊዜ የተከሰተው ግንቦት 15 ቀን 2013 ዓ.ም መሆኑ ተነግሯል፡፡
በተመስገን አለባቸው
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.