Fana: At a Speed of Life!

ሴኔቱ የዶናልድ ትራምፕ የክስ ሂደት የሚመራበትን ህግ አፀደቀ

አዲስ አበባ፣ ጥር 13፣ 2012 (ኤፍ.ቢ.ሲ) የአሜሪካ ተወካዮች ምክር ቤት የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ የክስ ሂደት የሚመራበትን ህግ አፀደቀ፡፡

ፕሬዚዳንት ትራምፕ ስልጣንን በአግባቡ ባለመጠቀም እና የኮንግረሱን ስራ በማስተጓጎል ክስ የቀረበባቸው ሲሆን፥ ትራምፕ በበኩላቸው ድርጊቱን አልፈፀምኩም ሲሉ የቀረበባቸውን ክስ ያጣጥላሉ፡፡

በዚህም ዶናልድ ትራምፕ በአሜሪካ ታሪክ ስልጣን ላይ እያሉ ክስ የቀረበባቸው ሶስተኛው ፕሬዚዳንት ሆነዋል፡፡

ዴሞክራቶች ከኋይት ሃውስ የህግ ባለሙያዎች ጋር የክስ ሂደቱን የሚሰማው አካል ገለልተኝነት እና ነፃ መሆን ላይ ከፍተኛ ክርክር ማድረጋቸው ተነግሯል፡፡

የክስ ሂደቱ ዛሬ ቀጥሎ የሚካሄድ ሲሆን፥ በዴሞክራቶች በኩል ክሱ እንደሚቀርብ እና ይህንን ተከትሎም መከላከያ ማቅረብ እና ጥያቄዎች እንደሚነሱ ተጠቁሟል፡፡

ሆኖም በሪፐብሊካን አባላት በብዛት የተያዘው ሴኔቱ ትራምፕን ጥፋተኛ በማድረግ ከስልጣን ያነሳቸዋል ተብሎ እንደማይጠበቅ እየተገለፀ ይገኛል፡፡

ከዚህ ባለፈም የክስ ሂደቱ ዋነኛ ጉዳይ የሆነው የምስክሮች ጉዳይ መቋጫ አለማግኘቱም ነው የተነገረው።

ምንጭ፡-ቢቢሲ

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.