የሀገር ውስጥ ዜና

ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ጋር ተወያዩ

By Tibebu Kebede

June 03, 2021

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 26 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የውሃ መስኖና ኢነርጅ ሚኒስትር ዶክተር ኢንጂነር ስለሺ በቀለ ከደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ሳልቫኪር ማያርዲት ጋር ተወያዩ፡፡

ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተላከ መልዕክት ለፕሬዚዳንት ሳልቫኪር አድርሰዋል፡፡

በዚህ ወቅትም ከፕሬዚዳንቱ ጋር በሁለትዮሽ፣ በህዳሴ ግድብ ድርድር፣ በትግራይ ክልል አጠቃላይ ሁኔታ፣ በኢትዮ ሱዳን የድንበር ሁኔታ እንዲሁም በመጭው ሃገራዊ ምርጫ ላይ ምክክር ማድረጋቸውን የደቡብ ሱዳን ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት መረጃ ያመላክታል፡፡

ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ የታችኛው የተፋሰሱን ሃገራት የመጉዳት ምንም አይነት ፍላጎት እንደሌላት አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ ባለፈም ከሃገራቱ የተውጣጣው የተመራማሪዎች ቡድን ግድቡ የትኛውም ሃገር ላይ ተፅዕኖ እንዳያሳድር የሚያስችል ስትራቴጅ መንደፉንም አስረድተዋል፡፡

ከመጭው ሃገራዊ ምርጫ ጋር በተያያዘም ምርጫው ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ እንደሚካሄድ ገልጸዋል፡፡

አያይዘውም መንግስት በተለያዩ የሃገሪቱ ክፍሎች ሊከሰቱ የሚችሉ ግጭቶችን ለማስወገድ እየሰራ ያለውን ስራ በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!