Fana: At a Speed of Life!

ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ምሥራቅ ምሥራቅ ሪጅን የ4ጂ አገልገሎት አስጀመረ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ኢትዮ ቴሌኮም በሰሜን ምሥራቅ ምሥራቅ ሪጅን አራት ከተሞች የአራተኛ ትውልድ (4ጂ)አገልገሎት አስጀመረ::
ኢትዮ ቴሌኮም በሠመራ፣ ሎጊያ፣ አሳይታ እና አዋሽ ሰባት ኪሎ ከተሞች ነው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ የሞባይል ኢንተርኔት አገልግሎት ማስፋፊያ ፕሮጀክት አጠናቆ አገልግሎቱን ማስጀመር የቻለው፡፡
የ4ጂ አገልግሎቱ የላቀ ፍጥነትና ባንድዊድዝ እንዲሁም አስተማማኝ የዳታ አገልግሎት የሚሰጥ በመሆኑ ደንበኞች አገልግሎቱን ዲጂታይዝ ለማድረግ፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና በአጠቃላይ የቴሌኮም አገልግሎት ላይ ያላቸውን ተሞክሮ በከፍተኛ ሁኔታ ለማሳደግ ያስችላቸዋል መባሉን ከድርጅቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
በቀጣይም ኩባንያው በተመሳሳይ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት የማስፋፊያ ሥራዎችን በማጠናቀቅ በተለያዩ የክልል ከተሞች አገልግሎቱን በቅርቡ ለማስጀመር የሚያስችሉ ቅድመ ሥራዎችን በማከናወን ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም እስካሁን ባደረጋቸው የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አገልግሎት ማስፋፊያ ስራዎች የሰሜን ምሥራቅ ምሥራቅ ሪጅንን ጨምሮ በአዲስ አበባ ፣ በደቡብ ምሥራቅ ሪጅን፣ በሰሜን ምዕራብ ሪጅን፣ በምሥራቅ ምሥራቅ ሪጅን፣ በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን፣ በምስራቅ ሪጅን፣ በማዕከላዊ ምስራቅ ሪጅን እና በሰሜን ምስራቅ ሪጅን በሚገኙ 44 ከተሞችን የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ለማድረግ ችሏል፡፡
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.