Fana: At a Speed of Life!

የትራንስፖርት ዘርፍ ስራዎች ችግር ፈቺ በሆኑ ጥናቶች ላይ መመስረት አለበት – የትራንስፖርት ሚኒስቴር

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ)የኢፌዴሪ የትራንስፖርት ሚኒስትር ወይዘሮ ዳግማዊት ሞገስ የትራንስፖርት ዘርፍ ካለው ሰፊ ተልዕኮ አንጻር ስራዎች ችግር ፈቺ በሆኑ ጥናቶች ላይ መመስረት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር በተለያዩ የጥናት ሰነዶች ላይ ውይይት አድርጓል።

በመድረኩ የገጠር መንገድ ትስስርና ተደራሽነት ፕሮግራም እንዲሁም የመንገድ መሰረተ ልማትን ለመቆጣጠርና ለመገምገም የሚያስችል ፕሮግራም ጥናት ቀርቦ የጥናት ሰነዶቹ ላይ ውይይት ተደርጎበታል።

በጥናቱ በኢትዮጵያ የሚገነቡ የመንገድ መሰረተ ልማቶችን እንዲሁም የሚሰጡ አገልግሎቶች ከመንገድ ደህንነት፣ ከግንባታና አገልግሎት፣ ዲዛይን፣ ከጥራት እንዲሁም ከአካባቢ ጥበቃ ዙሪያ የተሰሩ ስራዎችን ለመቆጣጠርና ለመገምገም የተዘረጋው ስርዓት ምንያህል ውጤታማ እንደሆነ ለመከታተል የሚያስችል ነው ተብሏል።

‘‘የገጠር ትስስርና ተደራሽነት ፕሮግራም’’ በሚል የመንገድ መሰረተ ልማትን ለማሳደግ አዲስ ፕሮግራም በኢትዮጵያ የመንገድ መሰረተ ልማትን ለማስተሳሰር የገጠር መንገዶችን ከማዕከላት ጋር ማስተሳሰር የሚያስችል ነው ተብሏል።

በተጨማሪም ፕሮግራሙ ተነጥለው ያሉ አካባቢዎችን ተደራሽ የሚያደርግ፣ የአርብቶ አደር አካባቢ የሚታዩ የመሸጋገሪያ ችግር የሚፈታና ድልድይ ግንባታ የሚጨምር እንደሆነም ነው የተጠቀሰው።

ሚኒስትሯ ጥናቶቹ ለቀጣይ የ10 ዓመታት የትራንስፖርት ዘርፍ ዕቅድ ስኬት አጋዥ መሆናቸውን አንስተዋል።

በውይይቱ የተገኙ ግብዓቶችን በማካተትና ተጨማሪ የመፍትሄ ሃሳቦችን በመጨመር ለረዥም ጊዜ ሊያገለግል በሚችል መልኩ እንዲዳብር በእያንዳንዱ ጥናቶች አንጻር ዝርዝር አቅጣጫ ሰጥተው በፍጥነት ተጠናቀው ተግባራዊ እንዲደርጉ ማሳሰባቸውን ከሚኒስቴሩ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.