Fana: At a Speed of Life!

የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ምክር ቤት ተመሠረተ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ምክር ቤት ተመሠረተ፡፡
ምክር ቤቱ ጥራቱን የጠበቀ ቀጣይነት ያለው የጥራት ባህል እንዲፈጠር ማድረግ የሚያስችል ገለልተኛ ነው ተብሏል፡፡
የሰለጠነ የሠው ሀይል፣ ለምርምር ብቁ የሆኑ ተመራማሪዎችን ማፍራት፣ በብቃትና በጥራት የሚመሩ አመራሮችና የሁሉንም ማህበረሰብ ህይወት መለወጥ የሚችሉ ተደራሽና ፍትሃዊ የሆነ የትምህርት ጥራትን የሚያስጠብቅ ምክር ቤት ለማድረግ ያለመ መሆኑም ታውቋል፡፡
የኢትዮጵያ ሙያ ማህበራት ፕሬዚዳንት ዶክተር ቢቂላ ወርቅነህ 20 30 በአፍሪካ የታወቀ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ምክር ቤት ለመሆን እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
በዚህ ወቅት በሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ሣሙኤል ኡርቃቶ በእውቀትና በክህሎት የዳበሩ ተማሪዎችና ተፈላጊነት ያላቸው ባለሙያዎችን ማፍራት ይጠበቅብናል ብለዋል።
የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ጂማ ዲቦ የከፍተኛ ትምህርት ጥራት ምክር ቤት ሰርተፍኬት ሰጥተዋል።
በሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በአዲስ አበባ ሣይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ግቢ ውስጥ ባዘጋጀው የምስረታ መርሃ ግብር ላይ የሣይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶክተር ሣሙኤል ኡርቃቶና ሌሎች የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል፡፡
በሰላም ተስፋዬ
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.