የሀገር ውስጥ ዜና

ለአረካ የግብርና ምርምር ልህቀት ማዕከል ግንባታ መሠረት ድንጋይ ተጣለ

By Meseret Awoke

June 04, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2013(ኤፍ ቢ ሲ) በወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ አረካ የግብርና ምርምር ልህቀት ማዕከል ግንባታ መሠረት ድንጋይ ተጣለ።

የመሰረተ ድንጋዩን የዩኒቨርሲቲው ምክትል ቦርድ ሰብሳቢ ዶክተር እንድሪያስ ጌታ እና የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ታከለ ታደሰ ያስቀመጡ ሲሆን፥ ለማዕከሉ የሚሆን 50 ሄክታር መሬት ከአረካ ከተማ ተበርክቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በመደበኛ እና በተከታታይ የትምህርት መርሐ ግብሮች ወደ 30 ሺህ የሚጠጉ ተማሪዎችን ተቀብሎ ያስተምራል።

በተመሳሳይ በአረካ ከተማ በ4 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ወጪ የተነባው የሀንጋዳ ጤና ጣቢያ በአምባሳደር ተሾመ ቶጋ ተመርቆ ተከፍቷል።

በተጨማሪም ከ16 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ የተደረገበት የአረካ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በዛሬው ዕለት ተመርቋል።

በማቱሳላ ማቴዎስና በመለሰ ታደለ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!