በተሳሳተ መልኩ ኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጫና ለመቀነስ እውነታውን የማስረዳት ሥራ በዳያስፖራው እየተከናወነ ነው – የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ
አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 27 ፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሰ)በተሳሳተ መልኩ ኢትዮጵያ ላይ የሚደረገውን ጫና ለመቀነስ እውነታን የማስረዳት ሥራ በዲያስፖራው እየተከናወነ መሆኑን የኢትዮጵያ ዲያስፖራ ኤጀንሲ ዋና ስራ አስኪያጅ ወይዘሮ ሰላማዊት ዳዊት አስታወቁ።
ዋና ሥራ አስኪያጇ በውጭ ሀገር እየተደረጉ ያሉ ጫናዎችን ከመከላከል አኳያ የፐብሊክ ዲፕሎማሲ ሥራ እንደሚያስፈልግ የገለጹ ሲሆን፥ ለዚህ የሚሆኑ ሥራዎች በዳያስፖራው ሲሰሩ ቆይተዋል ብለዋል።
ዳያስፖራው ከሰሞኑ አሜሪካ ያስተላለፈችውን ውሳኔ በመቃወም ሰልፍ በማድረግና በማህበራዊ ሚዲያ የተቃውሞ ዘመቻዎችን እያካሄደ መሆኑን አመልክተው፥ በየሀገሩ እየተካሄዱ ያሉ ሰልፎች ቀጣይነትም እንዳላቸው አስታውቀዋል።
የአሜሪካ እርምጃ የሁለቱን ሀገራት የረጅም ጊዜ መልካም ግንኙነትን ያላከበረ መሆኑን ያስታወቁት ወይዘሮ ሰላማዊት፥ ከኢትዮጵያ በኩል ያለውን እውነታ የማስረዳት ሥራ አሁንም በስፋት እየተሰራ ነው ብለዋል።
የህዳሴውን ግድብ አስመልክቶም በርካታ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ጫናዎችን መቀነስ ችለዋል ብለዋል።
በተጨማሪም በትግራይ ክልል ከተወሰደው የህግ ማስከበር ሂደት ጋር በተያያዘ በአሜሪካ የሚደረጉ ጫናዎችን ለመቋቋም ትክክል ባልሆኑ መረጃዎች አቋሞች ስለሚያዙ በመከታተል የማስተካከል ሥራ እየሰሩ እንደሆኑ መግለጻቸውን ኢፕድ ዘግቧል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!