የሀገር ውስጥ ዜና

የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከ50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ ድጋፍ ለተፈናቀሉ ዜጎች አደረገ

By Meseret Awoke

June 04, 2021

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 27፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በተለያዩ አካባቢዎች ለተፈናቀሉ ዜጎች ከ50 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የቁሳቁስ እርዳታ አድርጓል።

ሚኒስቴሩ በአጣዬ፣ ትግራይ እና መተከል አካባቢ በተለያዩ ወቅቶች ለተፈናቀሉ ዜጎች ነው እርዳታውን ያደረገው።

ለትግራይ ክልል የተደረገውን ድጋፍ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ ለአጣየ የደረገውን ባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር እንዲሁም የመተከሉን ጤና ሚኒስቴር እንደሚያስተባብሩ የዘገበው ኢቢሲ ነው።

ድጋፉ ቀጣይነት እንዲኖረውና የተፈናቀሉ ዜጎች ወደ ቀደመው ይዞታቸው እንዲመለሱ ሁሉም የበኩሉን እገዛ ማድረግ እንዳለበት የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናግረዋል።

ድጋፉ የሰራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከባህል እና ቱሪዝም እና የጤና ሚኒስቴር እንዲሁም ሌሎች አጋር አካላት ጋር በጋራ ያዘጋጁት ነው።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡- ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/ ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/ ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡ ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!