Fana: At a Speed of Life!

በትግራይ ክልል የጤና አገልግሎቶችን ለማጠናከርና ወደስራ ያልተመለሱትን ለመመለስ እየተሰራ ነው

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል የጤና አገልግሎቶችን ለማጠናከርና ወደስራ ያልተመለሱ ተቋማትን ለመመለስ ከአጋር ድርጅቶች ጋር እየተሰራ እንደሆን ጤና ሚንስቴር አስታወቀ።
ከኤጀንሲዎች፣ከትግራይ ክልል ጤና ቢሮ እና ከሰብዓዊና ልማት አጋሮች ጋር የሚሰራቸወ ስራዎች ተጠናክረው ቀጥለዋል፡፡
በክልሉ በአጠቃላይ ከሚገኙት ጤና ጣቢያዎች እና ሆስፒታሎች በአሁኑ ወቅት 46.5% የሚሆኑት አገልግሎት መስጠት እንዲችሉ ተደርጓል፡፡
በየጤና ተቋማቱ መድኃኒት እና የሕክምና መሳሪያ ለሟሟላት በተደረገው ጥረት የጤና ሚኒስቴር በመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ እንዲሁም ከሌሎች ተጠሪ ተቋማት ግምቱ ከብር 310 ሚሊዮን በላይ የመድሀኒትና የግብአት ድጋፍ ተደርጓል፡፡
ከሚኒስትር መስሪያ ቤቱ እና ኤጀንሲዎች ለተለያዩ የፕሮግራም ማስፈጸሚያ የሚውል በድምሩ ብር 215 ሚሊዮን 86 ሺህ 658.69 ጥሬ ገንዘብ እንዲተላለፍ ተደርጓዋል ተብሏል፡፡
በክልሉ ለተፈናቀሉ ወገኖች መሰረታዊ የጤና አገልግሎት በነጻ እንዲያገኙ እየተደረገ ሲሆን ቀደም ብለው ከነበሩት በተጨማሪ በክልሉ የሚገኙ 80 ሐኪሞች፤25 ነርሶች እንዲሁም 15 አዋላጅ ነርሶች ባለሙያዎች ቅጥር በጤና ሚኒስቴር ድጋፍ ተከናውኖ በሁሉም የተፈናቃይ ማእከላት በመመደብ ወደ ስራ እና ከፍተኛ ቁጥር ባለበት 17 መጠለያ መለስተኛ ክሊኒክ እንዲቋቋም መደረጉን ጤና ሚንስቴር በማህበራዊ ትስስር ገጹ አስፍሯል።
ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!
You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.