Fana: At a Speed of Life!

በመቐለ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት እንደሚጀምር ተገለፀ

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በመቐለ ከመጪው  ግንቦት 30፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት እንደሚጀምር ተገለፀ።

በመቐለ የመማር ማስተማር ሂደት እንዲቋረጥ ምክንያት የነበሩት ችግሮች መፍታታቸውን በመግለጽ፥ በሰባቱ ክፍለ ከተሞች በሚገኙ ትምህርት ቤቶች ከመጪው ሰኞ ጀምሮ ተማሪዎቻቸውን በመቀበል የትምህርት ሂደቱ እንደሚጀምሩ አስታውቋል።

የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ እንደገለፀው፥ ባለፈው ዓመት በሀገሪቱ ባጋጠመ የኮቪድ 19 ወረርሽኝ እንዲሆም ዘንድሮ በክልሉ በተፈጠረው የፀጥታ አለመረጋጋት ምክንያት ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ርቀው እነደነበር አሳታውሷል።

ዛሬና ነገ በከተማው የህዝብ ንቅናቄ ተግባራት የሚካሄድ ሲሆን፥ በዚህ እንቅስቃሴ የሚመለከታቸው አጋር አካላት በትብብር እንዲሰሩ ጥሪ አቅርቧል ሲል የትግራይ መገናኛ ብዙሃን ኤጀንሲ ዘግቧል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

 

 

 

 

 

 

 

 

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.