የሀገር ውስጥ ዜና

በትግራይ ክልል በሶስት ዙሮች ከ4.3 እስከ ለ4.5 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ ተደርጓል- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት

By Tibebu Kebede

June 05, 2021

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በትግራይ ክልል በሶስት ዙሮች ከ4.3 እስከ ለ4.5 ሚሊዮን ለሚሆኑ ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ መደረጉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታውቋል።

በመጀመሪያው ዞር ለ 4 ነጥብ 5 ሚሊዮን እንዲሁም በሁለተኛ እና በሶስተኛው ዙር ለ4 ነጥብ 3 ሚሊዮን ዜጎች የሰብአዊ ድጋፍ ተደርጓል ነው ያለው።

ከክልሉ በሦስት ዙሮችና አሁንም እየተካሄደ ባለው የሰብአዊ ድጋፍ ምግብ ነክ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ ድጋፎች መደረጋቸውን ከጽህፈት ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!