Fana: At a Speed of Life!

የደቡብ ክልል የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና መስጫ ጊዜ ይፋ ሆነ

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28፣ 2013 (ኤፍ ቢ ሲ) ክልላዊ የ8ኛ ክፍል ፈተና ከሰኔ 28 እስከ 30 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ የደቡብ ክልል ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የቢሮ ምክትል ኃላፊና የመማር ማስተማር ምዘና ዘርፍ ኃላፊ አቶ ገለቦ ጎልቶሞ ፥ ቢሮው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት በማድረግ የተማሪዎች መመዝገቢያ ቅጽ እንግሊዝ ሀገር ከሚገኝ ዲ.አር.ኤስ ድርጅት ግዢ እንደተፈጸመና ቢሮ መግባቱን ከደቡብ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ደርጅት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የቅጽ አሟላሉን በተመለከተ በክልሉ ላሉ ሁሉም የፈተና ክፍል ኃላፊዎች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መስጠቱን ተናግረዋል፡፡

በክልሉ የሚገኙ 16 ዞኖችና 7 ልዩ ወረዳዎች ፎርሙን ወስደው በመንግስትና በግል ፈተና የሚወስዱ ተማሪዎችን እያስሞሉ እንዳሉም አቶ ገለቦ ጎልቶሞ ገልፀዋል፡፡

የፈተና ዝግጅት ተጠናቆ የህትመት ስራ እየተሰራ ይገኛል ያሉት ኃላፊው፥ ፈተናው በክልሉ ሁሉም አካባቢዎች ከሰኔ 28 እስከ ሰኔ 30፣2013 ዓ.ም ይሰጣል ብለዋል፡፡

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-
ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/
ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting
ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/
ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision
ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡
ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.