Fana: At a Speed of Life!

2 ሚለየን 372 ሺህ ቶን ስኳር የማምረት አቅም ያለው የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ በነገው ዕለት ይመረቃል

 

አዲስ አበባ ፣ ግንቦት 28፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በግንባታ መዘግየትና የጥራት ችግር ውስጥ የነበረው የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ቁጥር አንድ  የ15ቀን የሙከራ የምርት ጊዜውን በማጠናቀቅ በነገው ዕለት ይመረቃል።

ፋብሪካው 2 ሚለየን 372 ሺህ ቶን ስኳር የማምረት አቅም እንደሚኖረው የተገለጸ ሲሆን፤ በቀን ከ160 ሺህ ቶን በላይ አገዳ  ይፈጫል።

የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ግንባታ ውስጥ ከሚገኙት የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ቁጥር አንድ  ግንባታው 2003 ዓ.ም በቀደመው የብረታብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ቢጀመርም በግንባታ ጥራት እና መዘግየት ችግር  2010 ዓ.ም ቀሪ የፋብሪካው  ግንባታ በ8 ወራት እንዲያጠናቅቅ ሥራውን ለቻይናው ካምሲ (ሲ ኤ ኤም ሲ) ኢንጂነሪንግ ኩባንያ በመስጠት  ግንባታውን ጀምሯል።

ኩባንያው አሁን ላይ ግንባታውን በማጠናቀቅ በ15 ቀን የሙከራ የምርት ጊዜው 200 ሺህ ኩንታል ስኳር በማምረት በነገው ዕለት የመንግስት ባለስልጣንና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት እንደሚመረቅ የጣና በለስ ስኳር ፋብሪካ ሥራ አስኪያጅ አቶ አንተነህ አስጌ  ለፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ተናግረዋል።

ከበለስ ወንዝ 30 ኪሎ ሜትር በተጠለፈ ውሃ አብዛኛው ማሣ ላይ በመርጨት መስኖ የሚጠጣ የሸንኮራ አገዳ ማሣ ያለው የስኳር ፋብሪካው፥ አሁን ላይ አጠቃላይ የለማ የሸንኮራ አገዳ ማሣ 13 ሺህ 667 ሄክታር ሲሆን ፣ ሙሉ በሙሉ ወደ ምርት ሲገባ 21 ሺህ ሄክታር  አጠቃላይ  የሸንኮራ አገዳ ማሣ እንደሚያስፈልገውም ሥራ አስኪያጁ  አያይዘው ገልጸዋል።

ሀገራዊ የስኳር አቅርቦት በዓመት 7 ሚሊዮን ኩንታል ነው የተመዘገበው አጠቃላይ ከፍተኛ የአገር ውስጥ የስኳር ምርት መጠን 4 ሚሊዮን ኩንታል በመሆኑ በፍላጎትና አቅርቦት መካከል ያለው ለመሙላት በዓመት ከ 2 እስከ 3 ሚሊዮን ኩንታል ስኳር ከውጪ እየገባ ለፍጆታ እንደሚውል መረጃዎች ያሳያሉ።

የጣና በለስ ስኳር ልማት ፕሮጀክት ጣና በለስ ቁጥር 1 ስኳር ፋብሪካ በአማራ ክልል አዊ ዞን ጃዊ ወረዳ የሚገኝ ነው።

በፀጋ ታሪኩ

ወቅታዊ፣ትኩስ እና የተሟሉ መረጃዎችን ለማግኘት፡-

ድረ ገጽ፦ https://www.fanabc.com/

ፌስቡክ፡- https://www.facebook.com/fanabroadcasting

ዩትዩብ፦ https://www.youtube.com/c/fanabroadcastingcorporate/

ቴሌግራም፦ https://t.me/fanatelevision

ትዊተር፦ https://twitter.com/fanatelevision በመወዳጀት ይከታተሉን፡፡

ዘወትር፦ ከእኛ ጋር ስላሉ እናመሰግናለን!

የተጀመረው

You might also like

Leave A Reply

Your email address will not be published.